ማርያም፣ የኢየሱስ እናት ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ; ዮሴፍ፣ የማርያም ባለቤት ተመልከቱ በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በስጋ ልጁ ለሆነው እናት እንድትሆን በእግዚአብሔ አብ የተመረጠች ድንግል። ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ፣ ማርያም ሌሎች ልጆች ወለደች (ማር. ፮፥፫)። እርሷ ለዮሴፍ ታጨች, ማቴ. ፩፥፲፰ (ሉቃ. ፩፥፳፯). ዮሴፍ ማርያምን እንዳይፈታ ወይም ከታጨችበት እንዳይለቃት ተነገረው, ማቴ. ፩፥፲፰–፳፭. ሰብአ ሰገል ማርያምን ጎበኙ, ማቴ. ፪፥፲፩. ማርያም እና ዮሴፍ ከሕጻኑ ኢየሱስ ጋር ወደ ግብፅ ሸሹ, ማቴ. ፪፥፲፫–፲፬. ከሄሮድስ ሞት በኋላ፣ ቤተሰቡ ወደ ናዝሬት ተመለሱ, ማቴ. ፪፥፲፱–፳፫. መልአኩ ገብርኤል ጎበኛት, ሉቃ. ፩፥፳፮–፴፰. ዘመድዋን ኤልሳቤጥን ጎበኘች, ሉቃ. ፩፥፴፮፣ ፵–፵፭. ማርያም ለጌታ የምስጋና መዝሙር አቀረበች, ሉቃ. ፩፥፵፮–፶፭. ማርያም ከዮሴፍ ጋር ወደ ቤተ ልሔም ሄደች, ሉቃ. ፪፥፬–፭. ማርያም ኢየሱስን ወለደች፥ በግርግም አስተኛችው, ሉቃ. ፪፥፯. እረኞች ህጻኑ ክርስቶስን ለመጎብኘት ወደ ቤተልሔም ሄዱ, ሉቃ. ፪፥፲፮–፳. ማርያም እና ዮሴፍ በኢየሩሳሌም ውስጥ ወደ ቤተመቅደስ ኢየሱስን ወሰዱ, ሉቃ. ፪፥፳፩–፴፰. ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስን ወደ ፋሲካ ወሰዱ, ሉቃ. ፪፥፵፩–፶፪. ማርያም በቃና ጋብቻ ላይ ነበረች, ዮሐ. ፪፥፪–፭. አዳኝ፣ በመስቀል ላይ እያለ፣ ዮሐንስን እናቱን እንዲንከባከብ ጠየቀ, ዮሐ. ፲፱፥፳፭–፳፯. ክርስቶስ ወደሰማይ ካረገ በኋላ ማርያም ከሐዋሪያት ጋር ነበረች, የሐዋ. ፩፥፲፬. ማርያም ከሌሎች ድንግሎች በላይ በጣም ውብ እና ቆንጆ የነበረች ድንግል ነበረች, ፩ ኔፊ ፲፩፥፲፫–፳. የክርስቶስ እናት ማርያም ተብላ ትጠራለች, ሞዛያ ፫፥፰. ማርያም ድንግል፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመሸፈን፣ የተከበረች እንዲሁም የተመረጠች ዕቃ ትሆናለች, አልማ ፯፥፲.