ማስተማር፣ አስተማሪ ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ተመልከቱ ለሌሎች፣ በልዩም ስለወንጌል እውነት፣ እውቀትን መስጠት እናም ወደ ጽድቅ መምራት። ወንጌልን የሚያስተምሩ በመንፈስ መመራት ይገባቸዋል። ሁሉም ወላጆች በቤተሰቦቻቸው መካከል አስተማሪዎች ናቸው። ቅዱሳን ከጌታ እና ከእርሱ መሪዎች ትምህርቶችን መፈለግ እና መቀበል ይገባቸዋል። ልጆቻቸውንም ያስተምሩ, ዘዳግ. ፬፥፰–፱. በትጋት ለልጆችህም አስተምረው, ዘዳግ. ፮፥፯ (ዘዳግ. ፲፩፥፲፰–፲፱). ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው, ምሳ. ፳፪፥፮. ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ, ኢሳ. ፶፬፥፲፫ (፫ ኔፊ ፳፪፥፲፫). መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን, ዮሐ. ፫፥፪. እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን, ሮሜ ፪፥፳፩. አባቴ ከሚያውቃቸው በመጠኑ ተማርኩ, ፩ ኔፊ ፩፥፩ (ኢኖስ ፩፥፩). ካህናትና መምህሮች በትጋት ያስተምሩ ወይም የህዝቡን ኃጢኣት በራሳችን ላይ ይቀበላሉ, ያዕቆ. ፩፥፲፰–፲፱. እኔን አዳምጡ፣ እናም ትሰሙኝ ዘንድ ጆሮአችሁን ክፈቱ, ሞዛያ ፪፥፱. ፲ልጆቻችሁ እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ እንዲሁም አንደኛው ሌላኛውን እንዲያገለግል ታስተምሯቸዋላችሁ, ሞዛያ ፬፥፲፭. ማንም የእናንተ መምህርም ሆነ አገልጋይ እንዲሆን አትፍቀዱ, ሞዛያ ፳፫፥፲፬. ጌታ የሰው ልጆችን ቃልን ለመቀበል ልባቸውን እንዲያዘጋጁ በምድሪቱ ላይ ሁሉ መንፈሱን አፈሰሰ, አልማ ፲፮፥፲፮. በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን አስተማሩ, አልማ ፲፯፥፪–፫. በእናቶቻቸውም ተምረዋል, አልማ ፶፮፥፵፯ (አልማ ፶፯፥፳፩). ጥበብን እስከፈለጉ ድርስ እንዲያስተምሯቸው, ት. እና ቃ. ፩፥፳፮. በሾምኳችሁ ስልጣን መሰረት እርስ በእርስ ተማማሩ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፳፫. በመጸሐፍ ቅዱስ እና በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኙትን የወንጌሌን መርሆች ያስተምራሉ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፪. ከበላይም መማር ይገባቸዋል, ት. እና ቃ. ፵፫፥፲፭–፲፮. ወላጆች ልጆቻቸውን ያስተምራሉ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭–፳፰. እርስ በራስ የመንግስትን ትምህርት አስተምሩ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፸፯–፸፰፣ ፻፲፰. ከመካከላችሁም አስተማሪ መድቡ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፪. ልጆችህን ብርሀን እና እውነት አላስተማርክም፤ እና ይህም የስቃይህ ምክንያት ነው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፴፱–፵፪. እነዚህን ነገሮች ለልጆቻችሁ አስተምሩ, ሙሴ ፮፥፶፯–፷፩. በመንፈስ ማስተማር በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁም, ማቴ. ፲፥፲፱–፳. መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን, ሉቃ. ፳፬፥፴፪. ወንጌሉ የሚሰበከው በመንፈስ ሀይል ነው, ፩ ቆሮ. ፪፥፩–፲፬. የተናገረውም በሀይል እና ከእግዚአብሔር በመጣ ስልጣን ነው, ሞዛያ ፲፫፥፭–፱ (አልማ ፲፯፥፫; ሔለ. ፭፥፲፯). ሰዎችን ለማሳመኛ መንፈሴን ትቀበላለህ, ት. እና ቃ. ፲፩፥፳፩. በአጽናኙ የምታስተምራቸው ነገሮች ሁሉ ትሰማለህ, ት. እና ቃ. ፳፰፥፩ (ት. እና ቃ. ፶፪፥፱). መንፈስን ካልተቀብላቹ አታስተምሩም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፬ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፮). በመንፈሴ ሀይል ለሰዎች ልጆች አስተምሩ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፲፭. ሽማግሌዎች ወንጌልን በመንፈስ ያስተምሩ, ት. እና ቃ. ፶፥፲፫–፳፪. በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ይሰጣችኋል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፹፭ (ት. እና ቃ. ፻፥፭–፰).