ስሚዝ፣ ጆሴፍ ቀዳማዊ ደግሞም ስሚዝ፣ ሉሲ ማክ; ስሚዝ፣ ጆሴፍ ዳግማዊ ተመልከቱ የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አባት። በሐምሌ ፲፪፣ ፲፯፻፸፩ (እ.አ.አ.) የተወለዱ ነበሩ። ሉሲ ማክን አገቡ፣ እናም እነርሱም ዘጠኝ ልጆች ወለዱ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፬)። ጆሴፍ በኋላኛው ቀን ዳግም መመለስ ታማኝ ሰው እና የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ፓትሪያርክ ሆኑ። በመስከረም ፲፬፣ ፲፰፻፵ (እ.አ.አ.) ሞቱ። እግዚአብሔር በልጁ ጆሴፍ በኩል መመሪያ ሰጠው, ት. እና ቃ. ፬፤ ፳፫፥፭. የሚሸመግለው አገልጋዬ፣ አሁን በሚኖርበት ቦታ ከቤተሰቡ ጋር ይቀጥል, ት. እና ቃ. ፺፥፳. የሚሸመግለው አገልጋዬ ጆሴፍ ከአብርሐም ጋር በቀኝ እጁ በኩል ተቀጥምጧል, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፲፱. ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ አባቱን በራዕይ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ አየ, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፭. መላእኩ ወደ አባቱ በመሄድ ስለመጀመሪያው ራዕይ እንዲነግረው ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን አዘዘ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፵፱–፶.