ቤተ ልሔም ከኢየሩሳሌም በደቡብ በአምስት ማይል (ስምንት ኪሎሜትር) የምትገኝ ከተማ። በእብራውያን ቋንቋ፣ ቤተ ልሔም “የዳቦ ቤት” ማለት ነው፤ ኤፍራታም ተብላ ትጠራለች፣ ይህም “ፍሬያማ”ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በቤተ ልሔም ነበር (ሚክ. ፭፥፪፤ ማቴ. ፪፥፩–፰)። የራሔል መቀበሪያ ቦታ ነው (ዘፍጥ. ፴፭፥፲፱፤ ፵፰፥፯)። ሩት እና ቦዔዝ በዚህችም ኖሩ, ሩት ፩፥፳፪. ሳሙኤል ዳዊትን በዚያ ቀባ, ፩ ሳሙ. ፲፮፥፩–፲፫፤ ፲፯፥፲፪፣ ፲፭፤ ፳፥፮፣ ፳፰. በዚያም ሄሮድስ ልጆችን አስገደለ, ማቴ. ፪፥፲፮.