ፋሲካ ደግሞም የመጨረሻው እራት; የእግዚአብሔር በግ ተመልከቱ የፋሲካ ድግስ የተጀመረው የእስራኤል ልጆች የሚያጠፋው መልአክ በቤቶቻቸው ላይ አልፎ እንደሄደ እና ከግብጾች እንዳዳናቸው እንዲያስታውሱ እንዲረዳቸው ነው (ዘፀአ. ፲፪፥፳፩–፳፰፤ ፲፫፥፲፬–፲፭)። በጥንት እስራኤልን ለማዳን ምልክት የነበሩ እንከን የሌላቸው በጎች፣ መስዋዕቱ የሰው ዘርን ያዳነ የእግዚአብሔር በግ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምልክት ነበሩ። ይህ የፋሲካ ሕግ ነው, ዘፀአ. ፲፪፥፵፫. ኢየሱስ እና ሐዋሪያቱ በመጨረሻው እራት ፋሲካን አከበሩ, ማቴ. ፳፮፥፲፯–፳፱ (ማር. ፲፬፥፲፪–፳፭). እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ, ዮሐ. ፩፥፳፱፣ ፴፮. ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና, ፩ ቆሮ. ፭፥፯. እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም ድናችኋል, ፩ ጴጥ. ፩፥፲፰–፲፱. የዓለምን ኃጢያት በወሰደው በእግዚአብሔር በግ እምነት ይኑራችሁ, አልማ ፯፥፲፬. የእስራኤል ልጆች እንደዳኑት፣ የጥበብ ቃልን በመከተል የሚኖሩ ቅዱሳን ይድናሉ, ት. እና ቃ. ፹፱፥፳፩. ከምድር መሰረት ጀምሮም በጉ ተገድሏል, ሙሴ ፯፥፵፯.