ልብ ደግሞም የተሰበረ ልብ; ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ተመልከቱ የሰው አዕምሮና ፍላጎት ምሳሌ እናም የስሜቶች ሁሉ ምሳሌአዊ ምንጭ። አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ, ዘዳግ. ፮፥፭ (ዘዳግ. ፮፥፫–፯; ማቴ. ፳፪፥፴፯; ሉቃ. ፲፥፳፯; ት. እና ቃ. ፶፱፥፭). እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል, ፩ ሳሙ. ፲፫፥፲፬. ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል, ፩ ሳሙ. ፲፮፥፯. እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ይወጣል እናም ይባረካል, መዝ. ፳፬፥፫–፭ (፪ ኔፊ ፳፭፥፲፮). በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና, ምሳ. ፳፫፥፯. ኤልያስ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል, ሚል. ፬፥፭–፮ (ሉቃ. ፩፥፲፯; ት. እና ቃ. ፪፥፪; ፻፲፥፲፬–፲፭; ፻፴፰፥፵፯; ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፰–፴፱). ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው, ማቴ. ፭፥፰ (፫ ኔፊ ፲፪፥፰). ሰው ከልብ መልካም ወይም ከልብ ክፉ መዝገብ ይናገራል, ሉቃ. ፮፥፵፭. በሙሉ ልባችሁ አላማ ወልድን ተከተሉ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፫. በመንፈስ ከእግዚአብሔር የተወለዳችሁ ናችሁን? በልባችሁስ ይህን ታላቅ ለውጥ ተለማምዳችኋልን, አልማ ፭፥፲፬. ለጌታ መስዋእት የተሰበረ ልብ እናም የተዋረደ መንፈስ ታቀርባላችሁ, ፫ ኔፊ ፱፥፳ (፫ ኔፊ ፲፪፥፲፱; ኤተር ፬፥፲፭; ሞሮኒ ፮፥፪). በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በአዕምሮህ እና በልብህ እነግርሃለሁ, ት. እና ቃ. ፰፥፪.