ወንጌል ሰባኪ ደግሞም የአባቶች አለቃ፣ ፓትሪያርክ; የፓትሪያርክ በረከቶች ተመልከቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መልካም ዜናን የሚያውጅ ወይም የሚወስድ ሰው። ጆሴፍ ስሚዝ ወንጌል ሰባኪ ፔትሪያርክ እንደሆነ አስተምሯል። ፔትሪያርኮች የተጠሩና በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት አመራር መሰረት የፔትሪያርክ በረከቶች ተብለው የሚጠሩ ልዩ በረከቶችን ለመስጠት የሚሾሙ ናቸው። ጌታ አንዳንዶቹን ሐዋርያት፣ ሌሎቹን ነቢያት፣ ሌሎቹን ወንጌልን ሰባኪዎች እንዲሆኑ ሰጠ, ኤፌ. ፬፥፲፩. የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ, ፪ ጢሞ. ፬፥፭. በሀዋርያት፣ በነቢያት፣ በሚኒስትሮች፣ በአስተማሪዎች፣ በወንጌል ሰባኪዎች እናምናለን, እ.አ. ፩፥፮.