አልሳዕ
የሰሜን እስራኤል መንግስት የብሉይ ኪዳን ነቢይ እና የሀገሯ የተለያዩ ንጉሶች የታመነ አማካሪ።
ኤልሳዕ አለቃው ኤልያስ የታወቀበት የሚንበለበል ጉጉት ሳይኖረው፣ የረጋና አፍቃሪ ጸባይ የነበረው ነበር። የእርሱ የሚጠቀሱት ታምራቶቹ (፪ ነገሥ. ፪–፭፤ ፰) በኤልያስ ምትክ ነቢይ ሲሆን (፪ ነገሥ. ፪፥፱–፲፪) በእውነትም የኤልያስን ሀይል እንደተቀበለ የሚመሰክሩ ነበሩ። ለምሳሌ፣ የሚመር ምንጭ ውሀን ፈወሰ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሀዎችን ከፋፈለ፣ የባልቴት ዘይትን አባዛ፣ ወንድ ልጅን ከሞት አስነሳ፣ ሰውን ከለምጽ ፈወሰ፣ የብረት ምሳር በውሀ ላይ እንዲንሳፈፍ አደረገ፣ እናም ሶሪያውያኖቹን አይነ ስውር አደረጋቸው (፪ ነገሥ. ፪–፮)። በኢዩራም፣ በኢዩ፣ በኢዮአካዝ፣ እና በኢዮአስም ንግስና ጊዜ ከሀምሳ አመት በላይ አገለገለ።