የጥናት እርዳታዎች
አሮናዊ ክህነት


አሮናዊ ክህነት

አነስተኛው ክህነት (ዕብ. ፯፥፲፩–፲፪ት. እና ቃ. ፻፯፥፲፫–፲፬)። ሀላፊነቶቹም ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህን፣ አስተማሪ፣ ዲያቆን ናቸው (ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፻፯፥፲፣ ፲፬–፲፭፣ ፹፯–፹፰)። በጥንት፣ በሙሴ ህግ በታች፣ ሊቀ ካህናት፣ ቄሶች፣ እና ሌዋውያኖች ነበሩ። የጥንት እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ ስላመጹ፣ ሙሴ እና ቅዱስ ክህነት ከእነርሱ ተወሰዱ እናም አነስተኛው ክህነት ቀጠለ። ለመቀደስ እና የመልከ ጼዴቅ ክህነትንና ስነስርዓቶቹን ለመቀበል እምቢ ብለው ነበር። (ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፫–፳፮ ተመልከቱ።) የአሮናዊ ክህነት በጊዜአዊ እና በህግ እና ወንጌል ውጪአዊ ስርዓቶችን ያስተዳድራል (፩ ዜና ፳፫፥፳፯–፴፪ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፮–፳፯፻፯፥፳)። የመልአክትን አገልግሎት፣ እና የንስሃ ወንጌልን እና የመጥመቅ ቁልፎችን ይዟል (ት. እና ቃ. ፲፫)። የአሮናዊ ክህነት በዚህ ዘመን ፍጻሜ ላይ በ፲፭ ግንቦት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ወደ ምድር ደግሞ ተመለሰ። መጥምቁ ዮሐንስ በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ አጠገብ ይህን በጆሴፍ ስሚዝ እና በኦሊቨር ካውደሪ ላይ አረጋገጠ (ት. እና ቃ. ፲፫ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፰–፸፫)።