ማቴዎስ
የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያ እና የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ መፅሐፍ ጸሀፊ። በቅፍርናሆም ውስጥ ለሮሜ ቀረጥ ይሰበስብ የነበረው አይሁድ ማቴዎስ ሄሮድስ አንቲጳስን የሚያገለግል ነበር። ከመቀየሩ በፊት እንደ እልፍዮስ ወንድ ልጅ ሌዋ ይታወቅ ነበር (ማር. ፪፥፲፬)። የኢየሱስ ደቀመዛሙርት እንዲሆን ከመጠራቱ በፊት፣ ጌታ የተገኘበት ድግስ ደገሰ (ማቴ. ፱፥፱–፲፫፤ ማር. ፪፥፲፬–፲፯፤ ሉቃ. ፭፥፳፯–፴፪)። ማቴዎስ ምናልባት የብሉይ ኪዳን ቅዱሣት መጻህፍቶች የተስፋፋ እውቀት ይኖረው ነበር እናም በጌታ ህይወት ውስጥ የትንቢት መሟላአትን ለማየት ችሏል። ስለሐዋሪያው የኋለኛው ህይወት የሚታወቀው ትንሽ ነው። አንድ ባህል እርሱ እንደ ሰማዕት ሞቷል ይላል።
የማቴዎስ ወንጌል
የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ መፅሐፍ። የማቴዎስ ወንጌል ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፈው በፍልስጥኤም ለሚገኙት አይሁዶች ጥቅም ነው። ከብሉይ ኪዳን ብዙ ጥቅሶችን ተጠቁሟል። የማቴዎስ ዋና አላማ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ነብያት የተናገሩበት መሲህ እንደሆነ ለማሳየት ነበር። ደግሞም ኢየሱስ የሰዎች ንጉስና ዳኛ እንደሆነ ትኩረት ሰጥቷል።
በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የተገለጹትን የአዳኝ ህይወት ድርጊቶችዝርዝር፣ የወንጌሎች ስምምነትን ተመልከቱ።