ሽንገላ (ውሸት)፣ መዋሸት፣ ማታለል ደግሞም ሐሰት; ተንኮል ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ማታለል ማለት አንድን ሰው እውነት ባልሆነ ነገር እንዲያምን ማድረግ ነው። ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ይወጣል, መዝ. ፳፬፥፫–፬. ከሸንጋይ አድነኝ, መዝ. ፵፫፥፩. ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ ወዮላቸው, ኢሳ. ፭፥፳ (፪ ኔፊ ፲፭፥፳). ማንም ራሱን አያታልል, ፩ ቆሮ. ፫፥፲፰. ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ, ኤፌ. ፭፥፮. ክፉ ሰዎች ያታልላሉም ይታለላሉም, ፪ ጢሞ. ፫፥፲፫. ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ሰይጣን ተጣለ, ራዕ. ፲፪፥፱. ሀገሮችን እንዳያታልል ዘንድ ሰይጣን ይያዛል, ራዕ. ፳፥፩–፫. ጌታ ሊታለል አይችልም, ፪ ኔፊ ፱፥፵፩. በእግዚአብሔር ፊት ባለማስመሰል ወልድን ብትከተሉ መንፈስ ቅዱስን ትቀበላላችሁ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፫. ሼረም በዲያብሎስ ሀይል እንደተታለለ ተናዘዘ, ያዕቆ. ፯፥፲፰. የንጉስ ኖህ ህዝቦች በድለላ ቃላት ተታልለው ነበር, ሞዛያ ፲፩፥፯. ጥበባኛው መንፈስ ቅዱስን እንደ መሪው ወስዷል፣ እናም አልተታለለም, ት. እና ቃ. ፵፭፥፶፯. አታላይ ለሆኑት ወዮላቸው, ት. እና ቃ. ፶፥፮. ለማታለል እና እንዳያዩ ለማድረግ፣ ሰይጣን፣ የውሸት አባት ሆነ, ሙሴ ፬፥፬.