መሰዊያ ደግሞም መስዋዕት ተመልከቱ ለመስዋዕት፣ ለቁርባን፣ እና ለአምልኮ የሚጠቀሙበት መሳሪያ። ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ እና መሥዋዕትን አቀረበ, ዘፍጥ. ፰፥፳. አብራም መሠውያን ለእግዚአብሔር ሠራ, ዘፍጥ. ፲፪፥፯–፰. አብርሐም ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው, ዘፍጥ. ፳፪፥፱ (ዘፍጥ. ፳፪፥፩–፲፫). ያዕቆብ በዛም መሰዊያ ሰራ እና ቦታውንም ቤቴል ብሎ ጠራ, ዘፍጥ. ፴፭፥፮–፯. ኤልያስ መሰዊያ ሰራ እና የበኣል ቄሶችን እንዲፎካከሩት ጠየቃቸው, ፩ ነገሥ. ፲፰፥፲፯–፵. መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፣ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ, ማቴ. ፭፥፳፫–፳፬. ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ, ራዕ. ፮፥፱ (ት. እና ቃ. ፻፴፭፥፯). ሌሒ የድንጋይ መሠዊያን ሠራ እና ለጌታ ለአምላካችን ምስጋና አቀረበ, ፩ ኔፊ ፪፥፯. አብርሐም ከኤልከናኽ መሰዊያ ላይ ከሞት ድኖ ነበር, አብር. ፩፥፰–፳.