ምኞት ደግሞም ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት ተመልከቱ ለአንድ ነገር ትክክል ያልሆነ ጠንካራ ፍላጎት መኖር ውበትዋን በልብህ አትመኘው, ምሳ. ፮፥፳፭. ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል, ማቴ. ፭፥፳፰ (፫ ኔፊ ፲፪፥፳፰). እንዲሁም ወንዶች እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ, ሮሜ ፩፥፳፯. እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ, ፪ ጢሞ. ፬፥፫–፬. ላባን ንብረታችን ባየ ጊዜ ተመኘው, ፩ ኔፊ ፫፥፳፭. በዓይንህ ምኞት ከእንግዲህ አትጓዝ, አልማ ፴፱፥፫–፬፣ ፱. ሴትን በምኞት የሚመለከት እምነትን ይክዳል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፫. ከፍተኛ ፍላጎታችሁን ሁሉ አቁሙ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፩.