እስጢፋኖስ እስጢፋኖስ በአዲስ ኪዳን ጊዜ ለአዳኝ እና ለቤተክርስቲያኑ ሰማዕት የነበረ ነበር። የእርሱ ስብከት፣ እስጢፋኖስ ሳንሀድሪን ፊት ሲከራከር በነበረበት ጊዜ እዚያ ለነበረው ጳውሎስ ታላቅ ስራ አስቀድሞ ያስመለከተ እና ምናልባት ተፅዕኖ የነበረው ነበር (የሐዋ. ፰፥፩፤ ፳፪፥፳)። እስጢፋኖስ አስራ ሁለቱን ሐዋሪያት እንዲረዱ ከተመደቡት ሰባት ሰዎች አንዱ ነበር, የሐዋ. ፮፥፩–፰. እስጢፋኖስም ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር, የሐዋ. ፮፥፰. እስጢፋኖስ ከአይሁዶች ጋር ይከራከር ነበር, የሐዋ. ፮፥፱–፲. ተከሰሰ፣ እናም በሳንሀድሪን ፊት ለፍርድ ቀረበ, የሐዋ. ፮፥፲፩–፲፭. እስጢፋኖስ መከራከሪያውን አቀረበ, የሐዋ. ፯፥፪–፶፫. መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ፣ አብና ወልድን በራዕይ አያቸው, የሐዋ. ፯፥፶፭–፶፮. ለምስክሩም እስጢፋኖስ ሰማዕት ሆነ, የሐዋ. ፯፥፶፬–፷.