ይቅርታ የሌለው ኃጢያት ደግሞም መስደብ; መንፈስ ቅዱስ; የጥፋት ልጆች; ግድያ ተመልከቱ መንፈስ ቅዱስን የመካድ ኃጢያት፣ ምህረት ለማግኘት የማይችል ኃጢያት። መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም, ማቴ. ፲፪፥፴፩–፴፪ (ማር. ፫፥፳፱; ሉቃ. ፲፪፥፲). ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው, ዕብ. ፮፥፬–፮. የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንም, ዕብ. ፲፥፳፮. በአንተ ውስጥ ስፍራ የነበረውን መንፈስ ቅዱስን የምትክድ ከሆነ፤ እናም እንደካድከው ካወቅህ፤ እነሆ፣ ይህ ይቅር የማይባል ኃጢያት ነው, አልማ ፴፱፥፭–፮ (ያዕቆ. ፯፥፲፱). የአብን አንድያ ልጅ ስለካዱት፣ እናም እርሱንም በራሳቸው ስለሰቀሉት ይቅርታ የላቸውም, ት. እና ቃ. ፸፮፥፴–፴፭. መንፈስ ቅዱስን መስደብ ግን አይሰረይለትም፣ በእዚያም አዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን ከተቀበላችሁ በኋላ እናንተ ንጹህ ደም በማፍሰስ የምትገድሉበት ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፮–፳፯.