የጌታ የወይን አትክልት ስፍራ ደግሞም እስራኤል; እርሻ ተመልከቱ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እርሻ የሚሰጥ ምሳሌ። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ የጌታ የወይን አትክልት ስፍራ በብዙ ጊዜ የእስራኤል ቤትን ወይም በምድር ላይ ያለውን የእግዚአብሔር መንግስት የሚጠቁም ነው። ይህ አንዳንዴም በአጠቃላይ ስለአለም ህዝቦች የሚጠቁም ነው። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው, ኢሳ. ፭፥፯ (፪ ኔፊ ፲፭፥፯). ኢየሱስ ስለወይን አትክልት ስፍራ አገልጋዮች ምሳሌ ሰጠ, ማቴ. ፳፥፩–፲፮. እስራኤልን በጌታ ወይን ስፍራውስጥ ከለማው የወይራ ዛፍ ጋር አመሳሰለ, ያዕቆ. ፭. የጌታ አገልጋዮች የወይን ስፍራውን ለመጨረሻ ጊዜ ይከረክማሉ, ያዕቆ. ፮. በወይኑ እርሻዬ የሚሰሩቱን በታላቅ በረከት እባርካቸዋለሁ, ት. እና ቃ. ፳፩፥፱ (አልማ ፳፰፥፲፬). በወይን አትክልት ስፍራዬ ለመጨረሻ ጊዜ ስሩ, ት. እና ቃ. ፵፫፥፳፰.