ቅዱሳት መጻህፍት
ያዕቆብ ፮


ምዕራፍ ፮

ጌታ እስራኤልን በመጨረሻው ቀን ይሰበስባል—ዓለም በእሳት ትቃጠላለች—ከእሳቱ ባህርና ከዲኑ ለመዳን ሰዎች ክርስቶስን መከተል ይኖርባቸዋል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን፣ እነሆ፣ ወንድሞቼ እተነብያለሁ ብዬ ለእናንተ እንደተናገርኩት እነሆ፣ ትንቢቴ ይህ ነው—የእስራኤልን ቤት በተመለከተ ከለማው ወይራ ዛፍ ጋር በማመሳሰል ነቢዩ ዜኖስ የተናገራቸው ነገሮች በእርግጥ ይሆናሉ።

እናም በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ህዝቡን ለማዳን እጁን የሚያነሳበት ቀን፣ አዎን፣ ለመጨረሻው ጊዜ እንኳን፣ የጌታ አገልጋይ ወደፊት በመቀጠል በኃይሉ የወይኑን ስፍራ የሚንከባከብበትና፣ የሚከረክምበት ቀን ነው፤ እናም ከዚያ በኋላ መጨረሻው በፍጥነት ይመጣል።

እናም በወይኑ ስፍራ በትጋት የሰሩት እንዴት የተባረኩ ናቸው፤ እናም ወደ ራሳቸው ስፍራስ የሚጣሉት እንዴት የተረገሙ ናቸው! እናም ዓለም በእሳት ትቃጠላለች

እናም የእስራኤልን ቤት ስሮችና ቅርንጫፎች ያስታወሰው አምላካችን እንዴት መሀሪ ነው፤ እናም ለእነርሱ ቀኑን ሙሉ ክንዱን ይዘረጋል፤ እነርሱም አንገተ ደንዳና እና ተቃዋሚ ህዝብ ናቸው፤ ነገር ግን አብዛኞቹም ልባቸውን ባያጠጥሩ በእግዚአብሔር መንግስት ይድናሉ።

ስለሆነም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ንስሀ እንድትገቡም፣ በልባችሁም ሙሉ ዓላማ እንድትመጡና፣ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደፀና እናንተም እንድትፀኑ በጥሞና ቃላት እለምናችኋለሁ። እናም በቀን ብርሃን የምህረት ክንዱ ወደ እናንተ በተዘረጋ ጊዜ ልባችሁን አታጠጥሩ።

አዎን፣ ዛሬ፣ ድምፁን ብትሰሙ፣ ልባችሁን አታጠጥሩ፤ ለምንስ ትሞታላችሁ?

እነሆም፣ ቀኑን ሁሉ በመልካሙ የእግዚአብሔርን ቃል ከተመገባችሁ በኋላ፣ መጥፎ ፍሬን አፍርታችሁ በመቆረጥ ወደ እሳት መጣል ይገባችኋልን?

እነሆ፣ እነዚህን ቃላት ትቃወማላችሁን? የነቢያቱን ቃላትስ ትቃወማላችሁን፤ ስለእርሱ ብዙዎች ከተናገሩ ከተባለ በኋላ፣ ክርስቶስን በተመለከተስ የተነገሩትን ቃላት ሁሉ ትቃወማላችሁን፤ እናም የክርስቶስን መልካም ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይልና፣ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታን ትክዳላችሁን፣ የቅዱስ መንፈስ እርካታንም ታጠፋላችሁን፣ እናም ለእናንተ የተመሰረተውን ታላቁን የቤዛነት ዕቅድ ትሳለቁበታላችሁን?

እነዚህን ነገሮች ካደረጋችሁ፣ በክርስቶስ ያለው የቤዛነትና የትንሳኤ ኃይል በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት በእፍረትና በመጥፎ ጸጸት እንደሚያቆማችሁ አታውቁምን?

እናም በፍርድ ኃይል መሰረት፣ ፍርድ ሊካድ አይችልምና፣ እናንተ በነበልባሉ ወደ ማይጠፋው፣ እናም ጢሱም ለዘለዓለም እስከዘለዓለም ወደሰማይ ወደሚወጣው፣ የእሳቱ ባህርና ዲን መጨረሻ የሌለው ስቃይ ወደሆነው፣ የእሳት ባህርና ዲን መሄድ ይገባችኋል።

፲፩ እንግዲህ አቤቱ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ንስሀ ግቡ፣ በጠባቡም ደጅ ግቡ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትን እስከምታገኙ ድረስ በቀጥተኛ ጎዳና ቀጥሉ።

፲፪ አቤቱ ብልህ ሁኑ፤ ከዚህ የበለጠ ምን ማለት እችላለሁ?

፲፫ በመጨረሻም ኃጢአተኞችን በመጥፎ ስጋትና ፍርሃት በሚመታው በአስደሳቹ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ እላችኋለሁ። አሜን።