በደል ደግሞም መጸጸት፣ ንስሀ መግባት ተመልከቱ ትክክል ያልሆነውን የማድረግ ሁኔታ፣ ወይም ከሃአጢያት ጋር የሚገኝ የጸጸት እና የሀዘን ስሜት። እርሱ ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ነው, ዘሌዋ. ፮፥፩–፮. ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት, ፩ ቆሮ. ፲፩፥፳፯. ጥፋተኞች እውነትን ከባድም አድርገው ይወስዱታል, ፩ ኔፊ ፲፮፥፪. ስለስህተቶቻችን ሁሉ ፍፁም እውቀት ይኖረናል, ፪ ኔፊ ፱፥፲፬. በደሌ ተወግዶልኛል, ኢኖስ ፩፥፮. ለሰዎች የህሊና ፀፀትን ለማምጣት የተመደበ ቅጣት ነበር, አልማ ፵፪፥፲፰. ኃጢያትህ ብቻ በዚያ ወደ ንስሃ በሚያመጣህ ጭንቀት ያስጨንቅህ, አልማ ፵፪፥፳፱. አንዳንዶቻችሁ በፊቴ ተጠያቂ ብትሆኑም፣ ነገር ግን ምህረትን አደርጋለሁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፲፬. የእግዚአብሔር ልጅ ለመጀመሪያው ኃጢያት ከፍሏል, ሙሴ ፮፥፶፬.