ደሀ ደግሞም ምፅዋት፣ የምፅዋት ስጦታ; በኩራት; በጎ ድርገት; ትሁት፣ ትሕትና; ጾም፣ መጾም ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ደሀ (፩) እንደ ምግብ፣ ልብስ፣ እና መጠለያ አይነት አስፈላጊ ነገሮች የሌላቸውን ሰዎች፣ ወይም (፪) ትሁት እና ትዕቢት የሌላቸው ሰዎችን ይጠቁማል። በአለማዊ እቃዎች ደሀነት በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ, ዘዳግ. ፲፭፥፯. በኃጢአተኛ ትዕቢት ድሀ ይናደዳል, መዝ. ፲፥፪. ለድሀ የሚሰጥ አያጣም, ምሳ. ፳፰፥፳፯. ድሆች ወደ ቤትህ አስገባ, ኢሳ. ፶፰፥፮–፯. ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ለድሆች ስጥ, ማቴ. ፲፱፥፳፩ (ማር. ፲፥፳፩; ሉቃ. ፲፰፥፳፪). እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን, ያዕ. ፪፥፭. ሀብታም በመሆናቸው ድሆችን ይጠላሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፴. ለኃጢአታችሁ ስርየትን እንድታገኙ የራሳችሁን ነገር ለድሃ ስጡ, ሞዛያ ፬፥፳፮. ለድሆች ከቁሳቁሶቻቸው አካፈሉ, አልማ ፩፥፳፯. የተቸገሩትን ካልረዳችሁ፣ ፀሎታችሁ ከንቱ ነው, አልማ ፴፬፥፳፰. ኔፋውያን ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው, ፬ ኔፊ ፩፥፫. ድሆችን ታስታውሳላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፴ (ት. እና ቃ. ፶፪፥፵). ልባችሁ ያልተሰበሩ ድሀ ሰዎችም ወዮላችሁ, ት. እና ቃ. ፶፮፥፲፯–፲፰. ድሀው ወደ በጉ ጋብቻ ይመጣሉ, ት. እና ቃ. ፶፰፥፮–፲፩. ኤጲስ ቆጶሱ የደሀዎችን ፍላጎት ለመርዳት መጓዝ ይገባዋል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፻፲፪. ድሀዎችን መንከባከብ የወንጌል ህግ ይመራል, ት. እና ቃ. ፻፬፥፲፯–፲፰. በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም, ሙሴ ፯፥፲፰. በመንፈስ ደሀነት በድሀነት ምክንያት ሳይገደዱ እራሳቸውን ትሁት የሚያደርጉ ከሌሎች በላይ የተባረኩ ናቸው, አልማ ፴፪፥፬–፮፣ ፲፪–፲፮. በመንፈስ ድሆች የሆኑ ወደ እኔም የሚመጡ ብፁአን ናቸው, ፫ ኔፊ ፲፪፥፫ (ማቴ. ፭፥፫). ለድሆች እና ትሁቶች ወንጌል ይሰበክላቸዋል, ት. እና ቃ. ፴፭፥፲፭.