ድንግል ደግሞም ማርያም፣ የኢየሱስ እናት ተመልከቱ የፍትወተ ስጋ ግንኙነት ፈፅመው የማያውቁ ለማግባት እድሜ የደረሰ ወንድ ወይም የደረሰች ሴት። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ድንግል ስነምግባር ጥሩ የሆነን ሰው የሚወክል ነው (ራዕ. ፲፬፥፬)። ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች, ኢሳ. ፯፥፲፬ (ማቴ. ፩፥፳፫; ፪ ኔፊ ፲፯፥፲፬). መንግስተ ሰማይ እንደ አስር ድንግሎች ተመሳስሏል, ማቴ. ፳፭፥፩–፲፫. በናዝሬትም ከተማ የእግዚአብሔር ልጅ እናት የሆነችን አንዲት ድንግል ተመለከትኩ, ፩ ኔፊ ፲፩፥፲፫–፲፰. ማርያም የተከበረች እንዲሁም የተመረጠች ዕቃ ናት, አልማ ፯፥፲.