የጥናት እርዳታዎች
ኢዩኤል


ኢዩኤል

በብሉይ ኪዳን ውስጥ በይሁዳ ምድር ውስጥ ነቢይ። የኖረበት ጊዜ በእርግጥ የታወቀ አይደለም—ከ፰፻፶ ም.ዓ. በፊት በኢዮአስ ዘመነ መንግስት እና የይሁዳ ጎሳ ከባቢሎን ምርኮ በመመለሳቸው መካከል ሳይኖር አይቀርም።

ትንቢተ ኢዩኤል

መፅሀፉ የይሁዳ ምድር በድርቀት እና በአንበጣዎች ከተመታ በኋላ ኢዩኤል በተነበያቸው ላይ ያተኩራል (ኢዩ. ፩፥፬–፳)። ኢዩኤል ህዝቡን ንስሀ ከገቡ በኋላ ከእግዚአብሔር በረከቶችን እንደሚያገኙ አረጋገጠላቸው (ኢዩ. ፪፥፲፪–፲፬)።

ምዕራፍ ፩ በጌታ ቤት ውስጥ ለክብር ስብሰባ ጥሪ ያለው ነው። ምዕራፍ ፪ ከአንድ ሺህ ዘመን በፊት ስለሚኖሩት ጦርነቶች እና ጥፋቶች ይናገራል። ምዕራፍ ፫ ስለኋለኛው ቀናት ይናረጋል እናም ሁሉም ሀገሮች በጦርነት ላይ እንደሚሆኑ ነገር ግን በመጨረሻም ጌታ በፅዮን እንደሚኖር ያረጋግጣል።

ጴጥሮስ በበዓለ ኀምሳ ቀን ስለነበረው የኢዩኤል የመንፈስ መገለፅ ትንቢትን ጠቅሷል (ኢዩ. ፪፥፳፰–፴፪የሐዋ. ፪፥፲፮–፳፩)። መልአኩ ሞሮኒም ይህን ትንቢት ለጆሴፍ ስሚዝ ጠቅሶለታል (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፵፩)።