ሰው፣ ሰዎች
ስለሁሉም የሰው ዘር፣ ወንድ እና ሴቶች፣ የሚናገር ነው። ሁሉም ወንዶችና ሴቶች የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች ናቸው። በሚሞት ሰውነት ሲወለዱ፣ ስጋዊና ሟች ሰውነቶችን ተቀበሉ። እነዚህ ሰውነቶች የተፈጠሩት በእግዚአብሔር መልክ ነበር (ዘፍጥ. ፩፥፳፮–፳፯)። አስፈላጊ የሆኑትን ስነስርዓቶች ለመቀበል ብቁ የሆኑ ወንዶች እና ሴቶች፣ ቃል ኪዳኖችን በማክበር፣ እናም የእግዚአብሔር ትእዛዛትን በማክበር ወደዘለአለማዊነታቸው ለመግባትና እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ይችላሉ።