ሰማዕት፣ ሰማዕትነት ክርስቶስን፣ ወንጌልን፣ ወይም ጻድቅ እምነቱን ወይም መሰረታዊ መርሆቹን ከመካድ ህይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው። ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ በክፉዎች ላይ ይመሰክራሉ, ማቴ. ፳፫፥፴፭ (ሉቃ. ፲፩፥፶). ስለ ክርስቶስና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያድናታል, ማር. ፰፥፴፭ (ት. እና ቃ. ፺፰፥፲፫). እስጢፋኖስን ወገሩት, የሐዋ. ፯፥፶፱ (የሐዋ. ፳፪፥፳). ኑዛዜ ያለ እንደሆነ የተናዛዡን ሞት ማርዳት የግድ ነው, ዕብ. ፱፥፲፮–፲፯. አቢናዲ በእሳት ሞቶ ወደቀ, ሞዛያ ፲፯፥፳. የተቀየሩት አሞኒሀውያን ወደ እሳት ተጣሉ, አልማ ፲፬፥፰–፲፩. ብዙዎች ስለእነዚህ ነገሮች በመመስከራቸው ተገድለዋል, ፫ ኔፊ ፲፥፲፭. ለምክንያቴ ህይወቱን የሚሰጥም ሰለአለማዊ ህይወትን ያገኘዋል, ት. እና ቃ. ፺፰፥፲፫–፲፬. ጆሴፍ ስሚዝ እና ሐይረም ስሚዝ በዳግም ለተመለሰው ወንጌል ሰማዕት ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፭. ጆሴፍ ስሚዝ ምስክሩን በደሙ አተመ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፱.