ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፭


ክፍል ፻፴፭

በሰኔ ፳፯፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) በካርቴጅ ኢለኖይ ውስጥ የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና የወንድሙ ፔትሪያርክ ሀይረም ስሚዝ ሰማዕትነትን ይፋ የሆነበት። ይህ መረጃ በ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ቅጂ ውስጥ መጨረሻ ላይ ተጨምሮ ነበር፣ ይህም ጆሴፍ እና ሀይረም ስሚዝ በተገደሉበት ጊዜ ለመታተም ተዘጋጅቶ ነበር።

፩–፪፣ ጆሴፍ እና ሀይረም በካርቴጅ እስር ቤት ሰማእት ሆኑ፤ ፣ የነቢዩ ከሁሉም በላይ የሆነው አቋም ተደነቀ፤ ፬–፯፣ ንጹህ ደማቸው የስራውን እውነትነት እና መለኮታዊነት ይመሰክራል።

የዚህን መፅሐፍ እና የመፅሐፈ ሞርሞንን ምስክር ለማተም፣ የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና የፔትሪያርክ ሀይረም ስሚዝ ሰማዕትነትን እናሳውቃለን። በሰኔ ፳፯፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ከሰአት በኋላ በአምስት ሰአት፣ ጥቁር የተቀቡ ከ፻፶ እስከ ፪፻ በሆኑ መሳሪያ በታጠቀ አመጸኛ ቡድን ሰዎች በካርቴጅ እስር ቤት ውስጥ በጥይት ተገደሉ። ሀይረም ነበር በመጀመሪያ በጥይት የተመታው እና በጸጥታም ሲወድቅ፣ የሞትኩኝ ሰው ነኝ! ብሎ በሀይል ተናገረ። ጆሴፍ ከመስኮት ዘለለ፣ እና ይህን ሲሞክርም በጥይት ተመታ፣ አቤቱ ጌታ አምላኬ! ብሎ በሀይል ተናገረ። ከሞቱም በኋላ በጥይቶችም ተመትተው ነበር፣ እና ሁለቱም በጭካኔ በአራት ጥይቶች ተመትተው ነበር።

በዚያን ጊዜ በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ከአስራ ሁለቱት አባላት ሁለቱ፣ ጆን ቴይለር እና ዊለርድ ሪቻርድ ብቻ ነበሩ፤ የመጀመሪያውም በጭካኔ በአራት ጥይቶች ተመትቶ ነበር፣ ነገር ግን ከዚህ በኋላም ድኗል፤ የኋለኛው በእግዚአብሔር ጥበቃ በልብሱም ላይ ቀዳዳ ሳይገኝ አመለጠ።

የጌታ ነቢይ እና ባለራዕይ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ከኢየሱስ በስተቀር፣ በዚህ አለም ውስጥ ለሰዎች ደህንነት ከኖሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ አድርጎታል። በአጭር በሆነ በሀያ አመት ጊዜ ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል የተረጎመውን መፅሐፈ ሞርሞንን አምጥቷል፣ እና በሁለት አህጉራት ላይ ይህን ለማተምም ምክንያት ሆኗል፤ ይህም የያዘውን የዘለአለም ወንጌል ሙላትን ወደ ምድር አራት ማዕዘናት ልኳል፤ ራዕያት እና ትእዛዛት የተቀናበሩበትን የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መፅሀፍን፣ እና ሌሎች ብዙ ብልህ መረጃዎችን እና መመሪያዎችንም ለሰዎች ልጆች ጥቅም አምጥቷል፤ ብዙ ሺህ የኋለኛ ቀን ቅዱሳንን ሰብስቧል፣ ታላቅ ከተማን መስርቷል፣ እና ሊሞት የማይችልን ታዋቂነትን እና ስምን ትቷል። በታላቅነት ኖሯል፣ እና በእግዚአብሔር እና በህዝቡ አይኖች ውስጥም በታላቅነት ሞቷል፤ እና እንደ ጥንቱም ጊዜ በጌታ እንደተቀቡ ብዙዎችም ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል፤ እና ወንድሙ ሀይረምም ይህንኑ አድርጓል። በህይወት አልተለያዩም ነበር፣ እና በሞትም አልተለያዩም!

ጆሴፍ ለህግ ጥያቄ ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ወደካርቴጅ ሲሄድ፣ ከመገደሉ ሁለት ወይም ሶስት ቀናት በፊት፣ እንዲህ ብሏል፥ “ለመታረድ እንደሚሄድ በግ እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እንደ በጋ ማለዳ የረጋሁ ነኝ፤ እግዚአብሔርን እና ለሁሉም ሰዎች ከማይጎዳ ንጹ ህሊናም አለኝ። በንፅህና እሞታለሁ፣ እና ስለ እኔ ግን እንዲህ ይባላል—ግድያ በታለመበት ተገደለ።”—በዚያም ማለዳ፣ ሀይረም ለመሄድ ከተዘጋጀ በኋላ—ወደ መታረድ ሊባል ይቻላልን? አዎን፣ ነበርና—በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በኤተር አስራ ሁለተኛ ምዕራፍ መጨረሻ አጠገብ ያለውን የሚቀጥለውን አንቀፅ አነበበ፣ እና ገጹንም አጠፈ፥

እናም እንዲህ ሆነ አህዛብ የጌታ ልግስና ይኖራቸው ዘንድ የመንፈስ ጥንካሬም እንዲያገኙ ወደ ጌታ ፀለዩ። እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ልግስና ከሌላቸው አንተ ታማኝ ስለሆንክ ላንተ ምንም አይደለም፤ ስለዚህ፣ ልብስህ ይነፃል። እናም ድካምህን በማየትህ በአባቴ ቤት ባዘጋጀሁልህ ስፍራ እንድትቀመጥ ብርቱ ተደርገሀል። እናም አሁን … አህዛብን አዎን እናም ደግሞ የምወዳቸው ወንድሞቼን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እስካገኛቸው ተሰናበትኳቸው፤ ሰዎችም ሁሉ ልብሶቼ በእናንተ ደም እንዳልተበከሉ ያውቃሉ። መስካሪዎቹ ሞተዋል፣ እና ምስክራቸውም ተፅዕኖ አለው።

ሀይረም ስሚዝ በሚያዝያ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) አርባ አራት አመቱ ነበር፣ እና ጆሴፍ ስሚዝ በታህሳስ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) ሰላሳ ስምንት አመቱ ነበር፤ እና ከዚህም በኋላ ስሞቻቸው ከሀይማኖት ሰማዕታት ጋር የተመደቡ ሆኑ፤ እና መፅሐፈ ሞርሞንን በሁሉም ሀገሮች ውስጥ የሚያነቡትም፣ እና ይህን የቤተክርስቲያኗ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መፅሐፍ የተበላሸውን አለም ወደ ደህንነት ለማምጣት በአስራ ዘጠነኛው መቶ አመት ከሁሉም የሚልቅ ደም እንደተከፈለበት ያስታውሱ፤ እና እሳት ለእግዚአብሔር ክብር አረንጓዴን ዛፍ የሚጎዳ ከሆነ፣ የተበላሸውን የወይን ስፍራ ለማፅዳት እንዴት በቀላል የደረቀውን ዛፍ ያነዳል። ለክብር ኖሩ፤ ለክብርም ሞቱ፤ እና ክብርም የዘለአለም ደመወዛቸው ነው። ከዘመን ወደ ዘመን እስከ ትውልድ ድረስ ስሞቻቸው ለተቀደሱት ዕንቁ ይሆናሉ።

ከዚህ በፊት እንዳረጋገጡት፣ በምንም ወንጀል ንጹህ ነበሩ፣ እና በከሀዲዎች እና በክፉ ሰዎች አድማ ብቻ ነበር የታሰሩት፤ እና በካርቴጅ እስር ቤት ወለል ላይ ንጹህ ደማቸው “በሞርሞንነት” ላይ በምድር ፍርድ ቤት ውስጥ ሊወገድ በማይቻል ማህተም የታተመ ነው፣ እና በስቴቱ አስተዳዳሪ የተገባው እምነት በመስበር፣ ንጹህ ደማቸውም ለኢለኖይ ስቴት ህጋዊ አልማም ነው፣ አለም ሁሉ ሊከሰው የማይችለው የዘለአለማዊ ወንጌል እውነትነት ምስክርም ነው፤ እና በነጻነት አርማ እና በዩናይትድ ስቴትስ ማግና ካርታ ላይ ንጹህ ደማቸው በሁሉም ሀገሮች መካከል ለሚገኙት የዋህ ሰዎች ለኢየሱስ ክርስቶስ ሀይማኖት አምባሳደር ነው፤ እና ንጹህ ደማቸውም ዮሐንስ ከመሰዊያው በታች ካያቸው ሰማዕታት ንጹህ ደም ጋር ወደ ሰራዊት ጌታ ያን ደም በምድር ላይ እስኪያበቅል ድረስ ይጮሀሉ። አሜን።