የወንጌል ዳግም መመለስ
እግዚአብሔር በምድር ላይ በሰዎች መካከል የወንጌሉን እውነት እና ስርዓቶችን እንደገና መመስረቱ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከክርስቶስ ሐዋሪያት አገልግሎት በኋላ በክህደት በኩል ጠፍቶ ነበር። ያም ክህደት የወንጌሉ ዳግም መመለስን አስፈላጊ አደረገ። በራዕዮች፣ በሚያገለግሉ መላእክቶች፣ እና በምድር ላሉት ሰዎች ራዕይ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ወንጌልን ዳግም መለሰ። ዳግም መመለስ የተጀመረው በጆሴፍ ስሚዝ ነበር (ጆ.ስ.—ታ. ፩፤ ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳–፳፩) እናም እስከ አሁን ድረስ በጌታ ህያው ነቢያት ስራዎች በኩል ቀጥሏል።