የጥናት እርዳታዎች
ዮናስ


ዮናስ

በጌታ ለነነዌ ከተማ ንስሀ መግባት እንዲሰብክ የተጠራ የብሉይ ኪዳን ነቢይ (ዮና. ፩፥፩–፪)።

ትንቢተ ዮናስ

ስለዮናስ ህይወት አጋጣሚ የሚናገር የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ። ምናልባት ዮናስ ይህን መፅሐፍን አልጻፈም ነበር። የትንቢተ ዮናስ ዋናው ሀሳብ ያህዌህ በማንኛውም ቦታ እንደሚነግስ እና ፍቅሩን ለአንድ ሀገር ወይም ህዝብ የሚገድብ አይደለም።

በምዕራፍ ፩ ውስጥ፣ ጌታ ዮናስን በነነዌ እንዲሰብክ ጠራው። ጌታ እንዳዘዘው በማድረግ፣ ዮናስ በመርከብ ሸሸ እናም በትልቅ አሳ ተዋጠ። በምዕራፍ ፪ ውስጥ፣ ዮናስ ወደ ጌታ ጸለየ፣ እና አሳው በድርቅ ምድር ላይ ዮናስን ተፋው። ምዕራፍ ፫ ዮናስ ወደ ነነዌ እንደሄደ እና የዚህን ውድቀት እንደተነበየ ይመዘግባል። ነገር ግን፣ ህዝቡ ንስሀ ገባ። ምዕራፍ ፬፣ ጌታ ህዝብን ስላዳነ በመናደዱ ጌታ ዮናስን ገሰጸ።

የዮናስ በአሳ መዋጡ እንደ ኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ አስቀድሞ የሚነግር እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ (ማቴ. ፲፪፥፴፱–፵፲፮፥፬ሉቃ. ፲፩፥፳፱–፴)።