በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ ከዳንኤል ጋር ወደ ባቢሎን ንጉስ ናቡከደነዖር ቤተመንግስት የተወሰዱ ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ነበሩ። የአብደናጎ ዕብራውያን ስም ዓዛርያስ ነበር። አራቱ ወጣት ሰዎች የንጉሱን ስጋ እና ወይን በመብላት እና በመጠጣት እራሳቸውን ለመበከል እምቢ አሉ (ዳን. ፩)። ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ ወደሚነደው ወደ እቶን እሳት ተጣሉ ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጅ በተአምራት ተጠብቀው ነበር (ዳን. ፫)።