መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞም አሮናዊ ክህነት; ኢልያ ተመልከቱ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የዘካሪያስ እና የኤልሳቤጥ ልጅ። ዮሐንስ ህዝብን ለመሲህ ለማዘጋጀት ተልኮ ነበር (ዮሐ. ፩፥፲፱–፳፯)። የአሮናዊ ክህነት ቁልፎች የያዘ ነበር እናም ኢየሱስ ክርስቶስን ጠመቀ። ኢሳይያስ እና ሌሎች ስለዮሐንስ ሚስዮን ተነበዩ, ኢሳ. ፵፥፫ (ሚል. ፫፥፩; ፩ ኔፊ ፲፥፯–፲; ፪ ኔፊ ፴፩፥፬). ወደ እስር ቤት ተሰደደ እናም ተሰየፈ, ማቴ. ፲፬፥፫–፲፪ (ማር. ፮፥፲፯–፳፱). ገብርኤል የዮሐንስን መወለድ እና አገልግሎት ለዘካሪያስ አስታወቀ, ሉቃ. ፩፥፭–፳፭. ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስ ታላቅ ነቢይ እንደነበረ አስተማረ, ሉቃ. ፯፥፳፬–፳፰. ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ አወቀው, ዮሐ. ፩፥፳፱–፴፬. የዮሐንስ ደቀ መዛሙርቶች የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች ሆኑ, ዮሐ. ፩፥፳፭–፳፱፣ ፴፭–፵፪ (የሐዋ. ፩፥፳፩–፳፪). ምንም ተአምራት አልሰራም, ዮሐ. ፲፥፵፩. ከሞት እንደተነሳ ሰው፣ ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውደሪን ወደ አሮናዊ ክህነት ለመሾም ተላከ, ት. እና ቃ. ፲፫ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፯–፰; ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፰–፸፪). በስምንት ቀን እድሜውም፣ በመልአክ ተሹሞ ነበር, ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፰.