የእምነት አንቀጾች
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባላት የሚደግፏቸው አስራ ሶስት የእምነት ነጥቦች።
ጆሴፍ ስሚዝ መጀመሪያ የጻፋቸው የቤተክርስትያኗ አባላት ምን እንደሚያምኑ ለማወቅ ለጠየቀው ለChicago Democrat [ቺካጎ ዴሞክራት ጋዜጣ] አዘጋጂ ለሆነው ጆን ወንትዎርዝ በመመለስ በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ነው። ደብዳቤው የወንትወርዝ ደብዳቤ ተብሎ ታወቀ እና ከመጀመሪያ ጊዜ በTimes and Seasons [በጊዜዎች እና በዘመናት] ውስጥ በመጋቢት ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.) ታትሞ ነበር። በጥቅምት ፲ ፲፰፻፹ (እ.አ.አ.)፣ የእምነት አንቀጾች በቤተክርስትያኗ አባላት ድምፅ መስጠት እንደ ቅዱሣት መጻህፍት በስነስርአታዊ ተቀባይ ሆነ እና በታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥም ተጨመረ።