የጥናት እርዳታዎች
የዮሐንስ ራዕይ


የዮሐንስ ራዕይ

ለሐዋሪያ ዮሐንስ የተሰጠውን ራዕይ የያዘ የአዲስ ኪዳን የመጨረሻ መፅሐፍ። የአለም ታሪክን፣ በተለይም የመጨረሻ ቀናትን፣ እንዲያይ ተፈቀደለት (ራዕ. ፩፥፩–፪፩ ኔፊ ፲፬፥፲፰–፳፯ት. እና ቃ. ፸፯)። የዮሐንስ ራዕይ ደግሞም አቡቃለምሲስ

ዮሐንስ ይህን ራዕይ የተቀበለው በጌታ ቀን፣ በእስያ ባህር ዳር፣ ከኤፌሶን ባልራቀው፣ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይ ነበር (ራዕ. ፩፥፱–፲)። የራዕዩ ትክክለኛ ቀን አይታወቅም።

ይህም መፅሐፍ የሚገባበት ቁልፎች በ፩ ኔፊ ፲፬፥፲፰–፳፯ እና በትምህርት እና ቃልኪዳኖች ፸፯ (ኤተር ፬፥፲፭–፲፮) ውስጥ ይገኛሉ።

ምዕራፍ ፩–፫ የመፅሐፉ ማስተዋወቂያ እና በእስያ ውስጥ ለሚገኙት ቤተክርስቲያናት ደብዳቤዎች ነበሩ። ዮሐንስ ደብዳቤውን የጻፈው ቅዱሳን ለአንዳንድ ችግሮችን መፍትሄ እንዲያገኙ ለመርዳት ነበር። ምዕራፍ ፬–፭ የእግዚአብሔርን እና የክርስቶስን ክብር እና ጻድቅ ሀይል የሚያሳዩ ራዕዮችን ዮሐንስ የተቀበለበትን ይመዘግባሉ። በምዕራፍ ፮–፱፲፩ ውስጥ፣ ዮሐንስ በሰባት መሀተማት የታተመ መፅሀፍን እንዳየ፣ እያንዳንዱም መሀተም የምድርን አንድ ሺህ ጊዜአዊ ታሪክን እንደሚወክል መዘገበ። እነዚህ ምዕራፎች በመጀመሪያ በሰባተኛው መሀተም ስለሚሆኑት ድርጊቶች ላይ ያተኩሩ ነበር (ራዕ. ፰–፱፲፩፥፩–፲፭ ተመልከቱ)። ምዕራፍ ፲ ዮሐንስ የበላውን መፅሀፍ ይገልጻሉ። ይህ መፅሀፍ ወደፊት የሚያከናውናቸው ተልዕኮን ይወክላል። ምዕራፍ ፲፪ ሰይጣን ሲያምጽ እና በተወረወረበት ጊዜ በሰማይ ስለተጀመረው ክፋት ራዕይ ይመዘግባል። በእዚያም የተጀመረው ጦርነት በምድር ላይ ቀጥሏል። በምዕራፎች ፲፫፲፯–፲፱ ውስጥ፣ ዮሐንስ ሰይጣን የሚቆጣጠረውን ኃጢያተኛ የምድር መንግስትን ገልጿል፣ እጣ ፈንታቸውን፣ በተጨማሪም የክፉን በመጨረሻ መደምሰስንም መዝግቧል። ምዕራፍ ፲፬–፲፮ ከክርስቶስ ዳግም ምፅዓት በፊት በኃጢያት መካከል የቅዱሳንን ጽድቅን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፳–፳፪ አንድ ሺህ አመትን፣ ውብታማዋን አዲሲቱን ኢየሩሳሌም፣ እና የምድርን ታሪክ የመጨረሻ ድርጊቶችን ይገልጻሉ።