ኑ ደግሞም ታዛዥነት፣ ታዛዥ፣ መታዘዝ; ደቀ መዛሙርት ተመልከቱ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ በአብዛኛው ጊዜ “ወደ ክርስቶስ ኑ እናም በእርሱም ፍጹማን ሁኑ” (ሞሮኒ ፲፥፴፪) በሚለው አይነት መግለጫ አንድን ሰው በመከተል ወይም ታዛዥ በመሆን መቅረብ ነው። ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ, ኢሳ. ፶፭፥፫. እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ, ማቴ. ፲፩፥፳፰. ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው, ማቴ. ፲፱፥፲፬. በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ, ሉቃ. ፱፥፳፫. ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም, ዮሐ. ፮፥፴፭. ክርስቶስ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል, ፪ ኔፊ ፳፮፥፴፫. ወደ እኔ ኑ እናም ዳኑ, ፫ ኔፊ ፲፪፥፳. ወደ ክርስቶስ ኑ, ሞሮኒ ፲፥፴፪. ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ጋብዙ, ት. እና ቃ. ፳፥፶፱. ወደ እኔ ኑ፣ እናም ነፍሳችሁ ይኖራል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፵፮.