ወራሽ ስጋዊ ወይም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመውረስ መብት ያለው ሰው። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ቅዱሳን እግዚአብሔር ላለው ሁሉ ወራሽ እንደምሚሆኑ ቃል ተገብቶላቸዋል። አብርሐም ወራሽን ፈለገ, ዘፍጥ. ፲፭፥፪–፭. አብርሃም የዓለምም ወራሽ የሆነው በእምነት ጽድቅ ነው, ሮሜ ፬፥፲፫. የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን, ሮሜ ፰፥፲፮–፲፯ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፰). ልጅ ነህ፣ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ, ገላ. ፬፥፯. እግዚአብሔር ልጁን የሁሉን ወራሽ አደረገ, ዕብ. ፩፥፪. ለኃጢአታቸው ስርየት ያንን ቀን የሚጠብቁ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ወራሾች ናቸው, ሞዛያ ፲፭፥፲፩. ሰዎች በአንድነት የክርስቶስ ልጆች፣ እናም የእግዚአብሔርንም መንግስት ወራሾች ነበሩ, ፬ ኔፊ ፩፥፲፯. ይህን ወንጌል ሳያውቁ የሞቱት ሁሉ የእግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት ወራሾች ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፯–፰. ንስሀ የገቡ ሙታን የደህንነት ወራሾች ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፰–፶፱. አብርሐም በጽድቅ መብት ያለው ወራሽ ሆነ, አብር. ፩፥፪.