ለምን ደግሞም ጸሎት ተመልከቱ እግዚአብሔርን ለልዩ ውለታ መጠየቅ፣ ጥያቄ ማቅረብ፣ ወይም አቤቱታ ማቅረብ። ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል, ማቴ. ፯፥፯. ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፣ …እግዚአብሔርን ይለምን, ያዕ. ፩፥፭ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፯–፳). በእምነት ጠይቁኝ, ፩ ኔፊ ፲፭፥፲፩. መረዳት ካልቻላችሁ፣ ይህም ስላልጠየቃችሁ ነው, ፪ ኔፊ ፴፪፥፬. ከልባችሁ ጠይቁ, ሞዛያ ፬፥፲. እግዚአብሔር ትክክለኛ የሆነውን ማንኛውንም ነገር በእምነት የምትጠይቁትን ይሰጣችኋል, ሞዛያ ፬፥፳፩. እነዚህ ነገሮች ሀሰት እንደሆኑ እግዚአብሔርን ጠይቁ, ሞሮኒ ፲፥፬. ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ይወዳሉ፤ ስለዚህም እኔን አይጠይቁም, ት. እና ቃ. ፲፥፳፩. እግዚአብሔርን ስለሁሉም ነገሮች እንድትጠይቁት ታዝዛችኋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፯.