ወደ ጢማቴዎች መልእክት
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሁለት መፅሐፎች። ሁለቱም በቅድሚያ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የጻፋቸው ደብዳቤዎች ነበሩ።
፩ ጢሞቴዎስ
ጳውሎስ የመጀመሪያውን መልእክት የጻፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ከታሰረ በኋላ ነበር። ጢሞቴዎስን በኋላ እንደገና ለመመለስ እያሰበ፣ በኤፌሶን ትቶት ሄዶ ነበር (፩ ጢሞ. ፫፥፲፬)። ነገር ግን፣ ጳውሎስ የሚዘገይ እንደሆነ ስላሰበ፣ ምናልባት ከመቄዶንያ፣ ምክር ለመስጠት እና ሀላፊነቱን ለማሟላት ለማበረታታት ወደ ጢሞቴዎስ ጻፈ (፩ ጢሞ. ፩፥፫)።
ምዕራፍ ፩ የጳውሎስን ሰላምታ እና ደግሞም በቤተክርስቲያኗ ለመገኘት ስለጀመሩት የሞኝነት ግምቶች መመሪያ የሰጠበትን የያዘ ነበር። ምዕራፍ ፪–፫ ስለህዝባዊ አምልኮ እና ስለአገልጋዮች ጸባይ እና አሰራር መመሪያ የሚሰጡ ነበሩ። ምዕራፍ ፬–፭ የኋለኛው ቀን ክህደትን መግለጫ እና የሚመራቸውን እንዴት ለማገልገል እንደሚችል ለጢሞቴዎስ የተሰጠን መመሪያ የያዙ ነበሩ። ምዕራፍ ፮ ታማኝ ለመሆን እና የአለም ሀብቶችን እንዲያስወግዱ የሚያበረታታ ነበር።
፪ ጢሞቴዎስ
ጳውሎስ ሁለተኛውን ደብዳቤ የጻፈው በታሰረበት በሁለተኛ ጊዜ፣ እና በስማዕቱ ከትንሽ ጊዜ በፊት ነበር። ይህም የሐዋርያውን የመጨረሻ ቃላት የያዘ እና ሞትን እንዴት በአስደናቂ ጉብዝና እና እምነት እንደተቋቋመ የሚያሳይ ነው።
ምዕራፍ ፩ የጳውሎስን ሰላምታ እና ለ ጢሞቴዎስ የሰጠውን ሀላፊነት የያዘ ነበር። ምዕራፍ ፪–፫ የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች እና መመሪያዎች፣ ወደፊት የሚመጡትን አደጋዊች ለመቋቋም ሀላፊነት የሚሰጡ ነበሩ። ምዕራፍ ፬ የሚክዱትን ምን ለማድረግ እንደሚችሉ ምክር የሰጠውን የያዘ የጳውሎስ ጓደኞች የተላከውን መልእክት የያዘ ነበር።