ምላስ ደግሞም የልሳኖች ስጦታ ተመልከቱ የንግግር ምሳሌ። ቅዱሳን ልሳናቸውን ይቆጣጠሩ፣ ይህም ማለት ንግግራቸውን ይቆጣጠሩ። ይህም ቋንቋዎችን ወይም ህዝቦችን ሊያመለክት ይችላል። በመጨረሻም፣ እያንዳንዱ ጉልበት ይንበረከካል እናም ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያምናል (ኢሳ. ፵፭፥፳፫፤ ሮሜ ፲፬፥፲፩)። አንደበትህን ከክፉ ከልክል, መዝ. ፴፬፥፲፫ (፩ ጴጥ. ፫፥፲). አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል, ምሳ. ፳፩፥፳፫. አንደበቱን ሳይገታ ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው, ያዕ. ፩፥፳፮. በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር ፍጹም ሰው ነው, ያዕ. ፫፥፩–፲፫. ወንጌሉ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰበካል, ራዕ. ፲፬፥፮–፯ (፪ ኔፊ ፳፮፥፲፫; ሞዛያ ፫፥፲፫፣ ፳; ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፫; ፻፲፪፥፩). ጌታ ለሀገሮች ሁሉ ቃሉን እንዲያስተምሩ የራሳቸውን ሀገር እና ቋንቋ ሰጥቷል, አልማ ፳፱፥፰. እነዚህ ሰሌዳዎች ለሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ህዝብ ይሄዳሉ, አልማ ፴፯፥፬. ቃሌን ለማግኘት ፈልግ፣ እናም ከዚያ አንደበትህ ይፈታል, ት. እና ቃ. ፲፩፥፳፩. በእራሱ ልሳን እያንዳንዱ ሰው የወንጌልን ሙላት ይሰማል, ት. እና ቃ. ፺፥፲፩.