የእውነተኛ ቤተክርስቲያን ምልክቶች ደግሞም ምልክት; የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን; የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመልከቱ በእግዚአብሔር ተቀባይነትን እንዳገኘ የሚያሳይ እና ጌታ ልጆቹ የበረከቱን ሙላት እንዲያገኙ የመሰረተው ቤተክርስቲያን ትምህርቶችና ስራዎች። የእውነተኛ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ምልክቶች የሚቀጥሉት ናቸው፥ የአምላክ ትክክለኛ እውቀት እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ, ዘፍጥ. ፩፥፳፮–፳፯. ጌታ ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ተነጋገረ, ዘፀአ. ፴፫፥፲፩. የዘለአለማዊ አባት እግዚአብሔርንና ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ነው, ዮሐ. ፲፯፥፫. አብና ወልድ የስጋና ኣጥንቶች ሰውነቶች አላቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፪–፳፫. አብና ወልድ በጆሴፍ ስሚዝ ታዩ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፭–፳. በዘለአለማዊው አብ፣ እግዚአብሔር እናምናለን, እ.አ. ፩፥፩. ቀዳሚ መሰረታዊ መርሆች እና ስነስርዓቶች ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር, ዮሐ. ፫፥፫–፭. ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ, የሐዋ. ፪፥፴፰. በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ, የሐዋ. ፰፥፲፬–፲፯. በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ, ገላ. ፫፥፳፮–፳፯. ንስሀ ግቡ፣ እናም በውዱ ልጄ ስም ተጠመቁ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፩–፳፩. ያመኑት ተጠመቁ እናም መንፈስ ቅዱስን እጆችን በመጫን ተቀበሉ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፶፫. ለመጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመስጠት ትክክለኛው ክህነት ያስፈልጋል, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፸–፸፪. የወንጌሉ ቀዳሚ መሰረታዊ መርሆችና ስነስርዓቶች ተገልጸዋል, እ.አ. ፩፥፬. ራዕይ ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል, ምሳ. ፳፱፥፲፰. እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለነቢያት ይነገራል, ዓሞ. ፫፥፯. ቤትክርስቲያኗ በራዕይ አለት ላይ ተገንብታለች, ማቴ. ፲፮፥፲፯–፲፰ (ት. እና ቃ. ፴፫፥፲፫). ጌታ ከእንግዲህ በራዕይ አይሰራም ለሚል ወዮለት, ፫ ኔፊ ፳፱፥፮. ራዕያትና ትእዛዛት የሚመጡት በተመደበው ብቻ ነው, ት. እና ቃ. ፵፫፥፪–፯. እግዚአብሔር በገለጸው ሁሉ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፱. ነቢያት በቤክርስቲያኗ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ተጸንሳለች, ኤፌ. ፪፥፲፱–፳. ሐዋሪያትና ነቢያት ለቤተክርስቲያኗ አስፈላጊ ናቸው, ኤፌ. ፬፥፲፩–፲፮. ጆሴፍ ስሚዝ ባለ ራዕይ፣ ነቢይ፣ እና ሐዋሪያ እንዲሆን ተጠራ, ት. እና ቃ. ፳፩፥፩–፫. በነቢያት እናምናለን, እ.አ. ፩፥፮. ስልጣን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሀይልና ስልጣን ሰጣቸው, ሉቃ. ፱፥፩–፪ (ዮሐ. ፲፭፥፲፮). የሔለመን ልጅ ኔፊ ከእግዚአብሔር ታላቅ ስልጣን ነበረው, ሔለ. ፲፩፥፲፰ (፫ ኔፊ ፯፥፲፯). ነቢያት ለቤትክርስቲያኗ ትእዛዛትን ይቀበሉ, ት. እና ቃ. ፳፩፥፬–፭. ስልጣን ባለው ካልተሾም በስተቀር ማንም ወንጌልን መስበክ ወይም ቤተክርስቲያኗን መገንባት አይችልም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፩. ሽማግሌዎች ወንጌልን በስልጣን በመስራት ይስበኩ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፰. የሚሰብክ ወይም ለእግዚአብሔር የሚያገለግል ማንም ሰው ስልጣን ባለው ሰው በኩል በእግዚአብሔር መጠራት አለበት, እ.አ. ፩፥፭. ተጨማሪ ቅዱሣት መጻህፍት ይመጣሉ የይሁድ በትር እና የዮሴፍ በትር ይጋጠማሉ, ሕዝ. ፴፯፥፲፭–፳. የኋለኛው ቀን ቅዱሳት መጻህፍት መምጣት ቀድሞ ተነግሮ ነበር, ፩ ኔፊ ፲፫፥፴፰–፵፩. እግዚአብሔር ታላቅና አስፈላጊ ነገሮች ወደፊት እንደሚገልፅ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፱. የቤተክርስቲያን ድርጅት በቤክርስቲያኗ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ተጸንሳለች, ኤፌ. ፪፥፲፱–፳. ሐዋሪያትና ነቢያት ለቤተክርስቲያኗ አስፈላጊ ናቸው, ኤፌ. ፬፥፲፩–፲፮. ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው, ኤፌ. ፭፥፳፫. የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በስሙ መጠራት አለባት, ፫ ኔፊ ፳፯፥፰. በድሮው ቤተክርስቲያን እንደነበረው አንድ አይነት ድርጅት እናምናለን, እ.አ. ፩፥፮. የሚስዮን ስራ እንግዲህ ሂዱና፣ እናም አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ, ማቴ. ፳፰፥፲፱–፳. ስብዓዎች ወንጌልን እንዲሰብኩ ተጠሩ, ሉቃ. ፲፥፩. ደህንነት ለሁሉም ፍጡር መታወጅ እንደሚገባው ፍላጎት ነበራቸው, ሞዛያ ፳፰፥፫. ሽማግሌዎች ይሂዱ፣ ሁለት በሁለትም ወንጌሌን ይስበኩ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፮. ወንጌሉ ለሁሉም ፍጥረቶች መሰበክ አለበት, ት. እና ቃ. ፶፰፥፷፬. መንፈሳዊ ስጦታ በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር, የሐዋ. ፪፥፬. ሽማግሌዎች የታመሙትን ይፈውሱ, ያዕ. ፭፥፲፬. የእግዚአብሔርን ስጦታ አትካድ, ሞሮኒ ፲፥፰. መንፈሳዊ ስጦታዎች ተዘርዝረዋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፲፫–፳፮ (፩ ቆሮ. ፲፪፥፩–፲፩; ሞሮኒ ፲፥፱–፲፰). ቤተመቅደሶች የዘላለምም ቃል ኪዳን እሰራለሁ፣ እናም መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ, ሕዝ. ፴፯፥፳፮–፳፯. ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል, ሚል. ፫፥፩. ኔፊ ቤተመቅደስ ሰራ, ፪ ኔፊ ፭፥፲፮. ቅዱሳን የጌታን ቤተ ባለመገንባታቸው ተገሰጹ, ት. እና ቃ. ፺፭ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፲፱). የጌታ ህዝቦች ቅዱስ ስነስርዓቶችን ለማከናወን ሁልጊዜም ቤተመቅደሶች ይገነባሉ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፴፯–፵፬. ቤተመቅደስን መገንባትና ስነስርዓቶችን ማከናወን የኋለኛው ቀን ታላቅ ስራ ክፍሎች ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፫–፶፬.