የጥናት እርዳታዎች
ቤተመቅደስ፣ የጌታ ቤት


ቤተመቅደስ፣ የጌታ ቤት

ቃል በቃል የጌታ ቤት ነው። ጌታ ህዝቡን ሁልጊዜም ብቁ ቅዱሳን የወንጌሉን ቅዱስ ስነስራአቶችን ለእራሳቸው እና ለሙታናቸው የሚያከናውኑበትን ቅዱስ ህንጻ የሆነውን ቤተመቅደስ እንዲገነቡ ያዝዛል። ጌታ ቤተመቅደሱን ይጊበኛል፣ እናም ከማምለኪያ ቦታዎች ሁሉ የተቀደሰ ነው።

በሙሴ እና በእስራኤል ልጆች የተሰራው ታቦት ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር የሚችል ቤተመቅደስ ነበር። እስራኤላውያን ከግብፅ በተሳደሱበት ጊዜ ይህን ተጠቀሙበት።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ታዋቂ ቤተመቅደስ በሰለሞን በኢየሩሳሌም ውስጥ የተገነባው ነው (፪ ዜና ፪–፭)። በ፭፻፹፯ ም.ዓ. በባቢሎን ተደምስሶ ነበር እናም ከ፸ አመት በኋላ በዘሩባቤል እንደገና ተገነባ (ዕዝ. ፩–፮)። የቤተመቅደሱ ክፍል በ፴፯ ም.ዓ. ተቃጥሎ ነበር፣ እናም ታላቁ ሄሮድስ በጓላም እንደገና ገነባው። ሮማውያን ቤተመቅደሱን በ፸ ዓ.ም. ደመሰሱት።

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የእግዚአብሔር ጻድቅ ተከታዮች ቤተመቅደሶችን እንዲገነቡ እና በእዚያም እንዲያመልኩ ተመርተው ነበር (፪ ኔፊ ፭፥፲፮ሞዛያ ፩፥፲፰፫ ኔፊ ፲፩፥፩)። በማንኛውን ዘመን፣ እንዲሁም በቀናችን በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ውስጥም፣ ቤተመቅደስን መገንባት እና በትክክል መጠቀም የእውነተኛ ቤተክርስቲያን ምልክቶች ናቸው። በዚህ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተመቅደስ ለጌታ የተገነባው እና የተቀደሰው የከርትላንድ ቤተመቅደስ ነበር። ከእዚያ ጊዜ በኋላም፣ በምድር ላይ ሁሉ በብዙ ቦታዎች ቤተመቅደሶች ተቀደሰው ነበር።