ሚካኤል ደግሞም አዳም; የመላእክት አለቃ ተመልከቱ ከምድራዊ ህይወት በፊት አዳም ይታወቅበት የነበረው ስም። እርሱም የመላእክት አለቃ ተብሎ ይጠራ ነበር። በአይሁዳ ቋንቋ ስሙ “እንደ እግዚአብሔር አይነት የሆነ” ማለት ነው። ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል፣ ዳንልን ለመርዳት መጣ, ዳን. ፲፥፲፫፣ ፳፩ (ት. እና ቃ. ፸፰፥፲፮). በመጨረሻው ቀናት ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል, ዳን. ፲፪፥፩. የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር ተከራከረ, ይሁዳ ፩፥፱. ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ, ራዕ. ፲፪፥፯ (ዳን. ፯). ሚካኤል አዳም ነው, ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፩ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፶፫–፶፯; ፻፳፰፥፳፩). የጌታ የመላእክቶቼ አለቃ ሚካኤል መለክቱን ይነፋል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፳፮. ሚካኤል ሰራዊቶቹን ይሰበስባል እናም ከሰይጣን ጋር ይዋጋል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፲፪–፻፲፭. የሚካኤል ድምፅም ዲያብሎስን ሲመረምር ተሰምቶ ነበር, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳.