መወለድ ደግሞም አንድያ ልጅ; የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች; የክርስቶስ ልጆች; ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ተመልከቱ መወለድ ወደ ህይወት ማምጣት በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ እነዚህ ቃላቶች ብዙም ጊዜ የሚጠቀሙባቸው ከእግዚአብሔር የመወለድን ለማለት ነው። ምንም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የአብ አንድያ ልጅ ቢሆንም፣ ሁሉም ሰዎች እርሱን በመቀበል፣ ትእዛዛቱን በማክበር፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በኩል አዲስ ሰዎች በመሆን ከክርስቶስ የተወለዱ ለመሆን ይችላሉ። እኔ ዛሬ ወለድሁህ፣ መዝሙረ ዳዊት, መዝ. ፪፥፯ (የሐዋ. ፲፫፥፴፫; ዕብ. ፩፥፭–፮; ፭፥፭). አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ነው, ዮሐ. ፩፥፲፬ (፪ ኔፊ ፳፭፥፲፪; አልማ ፲፪፥፴፫–፴፬; ት. እና ቃ. ፸፮፥፳፫). እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል, ዮሐ. ፫፥፲፮ (ት. እና ቃ. ፳፥፳፩). ክርስቶስ ህዝቦቹን በመንፈስ ወልዷቸዋል, ሞዛያ ፭፥፯. በጌታ በኩል የተወለዱት የበኩር ቤተክርስቲያን ናቸው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፪.