የጥናት እርዳታዎች
መቀባት


መቀባት

በጥንት ጊዜያት፣ የጌታ ነቢያት እንደ አሮን ወይም ካህናት ወይም እስራኤልን የሚገዙትን ንጉሶች አይነት ልዩ ሀላፊነቶች የሚያከናውኑትን በዘይት ይቀቡ ነበር። በዛሬ ቤተክርስትያን ውስጥ፣ መቀባት ማለት ትንሽ የተቀደሱ ዘይትን በሰው ጭንቅላት ላይ እንደ ልዩ በረከት ክፍል ማስቀመጥ ነው። ይህም መደረግ የሚቻለው በመልከ ጼዴቅ ክህነት ሀይል እና ስልጣን በኩል ብቻ ነው። ከቅባት በኋላ፣ የእዛ አይነት ክህነት ያለው ሰው ቅባትን ያትማል እና ልዩ በረከት ለተቀባው ይሰጣል።