አማኑኤል
ከኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች አንዱ። ይህም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራውያን ቃል የመጣ ነው።
አማኑኤል እንደ እግዚአብሔር ቤዛነት ምልክት የተሰጠ ስም-ርዕስ ነው (ኢሳ. ፯፥፲፬)። ኢሳይያስ የጠቀሰው አማኑኤል እንደ ኢየሱስ በስጋ መወለድ ትንቢት በማቴዎስ ተጠቁሟል (ማቴ. ፩፥፲፰–፳፭)። ስሙም በኋለኛው ቀን ቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ ታይቷል (፪ ኔፊ ፲፯፥፲፬፤ ፲፰፥፰፤ ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳፪)።