ትጋት የማይቋረጥ፣ ደፋር ጥረት፣ በልዩም ጌታን በማገልገልና ቃላቱን በማክበር። በትጋት አድምጡኝ, ኢሳ. ፶፭፥፪. እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ ይሰጣል, ዕብ. ፲፩፥፮. ትጋትን ሁሉ አሳዩ፣ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ, ፪ ጴጥ. ፩፥፭. የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት አስተምር, ያዕቆ. ፩፥፲፱. ቅዱሳን መጻሕፍትን በትጋት የሚያጠኑ ሰዎች ነበሩ, አልማ ፲፯፥፪. ባላቸው ትጋት ሁሉ የጌታን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ፈቃደኞች ነበሩ, ፫ ኔፊ ፮፥፲፬. እኛ ተግተን እንስራ, ሞሮኒ ፱፥፮. ጥሩ ስራን በጉጉት እናከናውን, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፯. ስራ ሳትፈቱ፣ በአቅማችሁ ሁሉ እየሰራችሁ እንድትሄዱ ፍላጎቴ ነው, ት. እና ቃ. ፸፭፥፫. ለዘለአለም ህይወት ቃላቶችም በትጉነት አዳምጡ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፫. እያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱን ይማር፣ እናም በትጋትም ይስራ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፺፱.