የመልከ ጼዴቅ ክህነት
የመልከ ጼዴቅ ክህነት ከፍተኛው ወይም ታላቁ ክህነት ነው፤ የመልከ ጼዴቅ ክህነት የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ በረከቶች ቁልፎችም ያለው ነው። በከፍተኛው ክህነት ስነስርዓቶች በኩል የአምላክነት ሀይል በሰው የሚገለፅበት ነው (ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፰–፳፭፤ ፻፯፥፲፰–፳፩)።
እግዚአብሔር ይህን ከፍተኛ ክህነት ለአዳም ገለጸ። በሁሉም ዘመናት የአባቶች አለቃዎችና ነቢያት ይህ ስልጣን ነበራቸው (ት. እና ቃ. ፹፬፥፮–፲፯)። በመጀመሪያ ይህም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱስ ክህነት ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህም በኋላ እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ታወቀ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፪–፬)።
የእስራኤል ልጆች ለመልከ ጼዴቅ ክህነት መብቶችና ቃል ኪዳኖች ብቁ ባልሆኑበት ጊዜ፣ ጌታ ከፍተኛውን ህግ ወሰደ እናም ዳግማዊን ክህነትና ዳግማዊን ህግ ሰጣቸው (ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፫–፳፮)። እነዚህም የአሮናዊ ክህነትና የሙሴ ህግጋት ተብለው ይጠሩ ነበር። ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ለአይሁዶች ደግሞም መለሰ እናም በመካከላቸውም ቤተክርስቲያኗን እንደገና መገንባት ጀመረ። ነገር ግን፣ ክህነት እና ቤተክርስቲያኗ በክህደት ምክንያት እንደገና ጠፉ። በኋላም እነዚህ በጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ በኩል በዳግም ተመለሱ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪–፲፫፤ ፻፳፰፥፳፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፸፫)።
በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ የሽማግሌዎች፣ የሊቀ ካህናት፣ የፓትሪያርክ፣ የሰባዎች፣ እና የሐዋርያ ሀላፊነቶች ይገኛሉ (ት. እና ቃ. ፻፯)። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ሁልጊዜም በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስት ክፍል ይሆናል።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት የከፍተኛው ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ፕሬዘደንት ነው፣ እናም በምድር ላይ ያለችው የእግዚአብሔር መንግስትን በሚመለከት ሁሉንም ቁልፎች የያዘ ነው። የፕሬዘደንትነት ጥሪ የሚያዘው በአንድ ጊዜ በአንድ ሰው ብቻ ነው፣ እና በምድር ላይ የክህነት ቁልፎችን በሙሉ ለመጠቀም ስልጣን ያለው እርሱም ብቻ ነው (ት. እና ቃ. ፻፯፥፷፬–፷፯፤ ፻፴፪፥፯)።