የጥናት እርዳታዎች
ብርሀን፣ የክርስቶስ ብርሀን


ብርሀን፣ የክርስቶስ ብርሀን

በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር የሚመጡ እና ህይወትና ብርሀን ለሁሉም ነገሮች የሚሰጡ መለኮታዊ ሀይል ወይም ተፅዕኖ። በሰማይ እና በምድር ላይ ሁሉም ነገሮች የሚመሩበት ህግ ነው (ት. እና ቃ. ፹፰፥፮–፲፫)። ይህም ደግሞ ሰዎች የወንጌል እውነትን እንዲያስተውሉ ይረዳል እናም ወደ ደህንነት በሚመራው የወንጌል መንገድም ይረዳቸዋል (ዮሐ. ፫፥፲፱–፳፩፲፪፥፵፮አልማ ፳፮፥፲፭፴፪፥፴፭ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፰–፳፱፣ ፴፩–፴፪፣ ፵፣ ፵፪)።

ዮሐንስ የክርስቶስ ብርሀን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መምታታት አይገባውም። የክርስቶስ ብርሀን ሰው አይደለም። ይህም ከእግዚአብሔር የሚመጣና ሰውን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የሚያዘጋጅ ተፅዕኖ ነው። በሰዎች ህይወት ላይ ሁሉ ለጥሩ ተፅዕኖ ያለው ነው (ዮሐ. ፩፥፱ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፮–፵፯)።

የክርስቶስ ብርሀን የሚታይበት አንዱ መንገድ ህሊና ነው፣ ይህም ሰው በትክክልና በስህተት መካከል እንዲመርጥ ይረዳል (ሞሮኒ ፯፥፲፮)። ሰዎች ስለወንጌል በተጨማሪ ሲማሩ፣ ህሊናቸው ስሜት በቀላል የሚሰማው ይሆናል (ሞሮኒ ፯፥፲፪–፲፱)። የክርስቶስ ብርሀንን የሚያዳምጡ ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ይመራሉ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፵፮–፵፰)።