የጥናት እርዳታዎች
ስሚዝ፣ ሀይረም


ስሚዝ፣ ሀይረም

የጆሴፍ ስሚዝ ታላቅ ወንድም እና ታማኝ ጓደኛ። በየካቲት ፱፣ ፲፰፻ (እ.አ.አ.) ተወልዶ ነበር። የቤተክርስቲያኗ ሁለተኛ ፓትሪያርክ ከመሆን በተጨማሪ፣ እርሱ በቤተክርስቲያኗ አመራር ውስጥ እንደ ጆሴፍ ረዳት አገለገለ። በሰኔ ፳፯፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.)፣ በካርቴጅ እስር ቤት ውስጥ ከጆሴፍ ጋር ሰማዕት ሆነ።