የጥናት እርዳታዎች
ኢየሱስ ክርስቶስ


ኢየሱስ ክርስቶስ

(የግሪክ ቃል የሆነው) ክርስቶስ እና (የዕብራዊያን ቃል የሆነው) መሲህ “የተቀባ” የሚል ትርጉም አላቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ በመንፈስ የበኩር ልጅ ነው (ዕብ. ፩፥፮ት. እና ቃ. ፺፫፥፳፩)። እርሱም በስጋ የአብ አንድያ ልጅ ነው (ዮሐ. ፩፥፲፬፫፥፲፮)። እርሱም ያህዌህ ነው (ት. እና ቃ. ፻፲፥፫–፬) እናም ለታላቁ ጥሪው ምድር ከመፈጠሯ በፊት ቀድሞ የተመረጥ ነበር። በአብ አመራር ስር፣ ኢየሱስ ምድርን እና በላዩዋ ያሉትን ሁሉ ፈጠረ (ዮሐ. ፩፥፫፣ ፲፬ሙሴ ፩፥፴፩–፴፫)። በቤተልሔም ከማርያም ተወለደ፣ ኃጢያት የሌለው ህይወት ኖረ፣ እናም ደሙን በማፍሰስ እና ህይወቱን በመስቀል ላይ አሳልፎ በመስጠት ለሰው ዘር ፍጹም የኃጢያት ክፍያን አደረገ (ማቴ. ፪፥፩፩ ኔፊ ፲፩፥፲፫–፴፫፫ ኔፊ ፳፯፥፲፫–፲፮ት. እና ቃ. ፸፮፥፵–፵፪)። ከሞት ተነሳ፣ በዚህም የሰው ዘር ሁሉ ከሞት እንደሚነሳ አረጋገጠ። በኢየሱስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ፣ ለኃጢያታቸው ንስሀ የሚገቡት እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚያከብሩ ከኢየሱስ እና ከአብ ጋር ለዘለአለም ለመኖር ይችላሉ (፪ ኔፊ ፱፥፲–፲፪፳፩–፳፪ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፶፫፣ ፷፪)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከምድር ላይ ከተወለዱት ሁሉ በላይ ታላቅ ነው። ህይወቱም የሰው ዘር ሁሉ መኖር ያለበት ፍጹም ምሳሌ ነው። ሁሉም ጸሎቶች፣ በረከቶች፣ እና የክህነት ስነስርዓቶች በእርሱ ስም መከናወን ይገባቸዋል። እርሱም የጌቶች ጌታ፣ የንጉሶች ንጉስ፣ ፈጣሪ፣ አዳኝ፤ እና የምድር ሁሉ አምላክ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሺህ አመት በሀይልና በክብር በምድር ላይ ለመንገስ እንደገና ይመጣል። በመጨረሻም ቀን፣ የሰው ዘርን ሁሉ ይፈርድባቸዋል (አልማ ፲፩፥፵–፵፩ጆ.ስ.—ማቴ. ፩)።

የህይወቱ ማጠቃለያ (በድርጊቶች ተከታታይነት)

ስለኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ እና ሞት ትንቢቶች

ስለኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠ ምስክር

ስልጣን

ክርስቶስ ከሟችነት በኋላ መገለጡ

የቤተክርስትያኗ ራስ

የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ

የክርስቶስ ምሳሌዎች እና ምልክቶች

የክርስቶስ ቅድመ ምድራዊ ህይወት

የክርስቶስ ክብር

የክርስቶስ የአንድ ሺህ አመት ግዛት

የክርስቶስን ስም በራሳችን ላይ መውሰድ

ዳኛ