አመጽ ደግሞም ኃጢያት; ማጉረምረም; ክህደት; ዲያብሎስ ተመልከቱ በእርሱ የተመረጡትን መሪዎች ለመከተል እምቢ በማለት እና ትእዛዛቱን በፈቃደኝነት ባለማክበር የጌታን ትእዛዝ መጣስ ወይም እርሱን መቃወም። በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ, ዘኁል. ፲፬፥፱. ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል, ምሳ. ፲፯፥፲፩. ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው, ኢሳ. ፴፥፩. ጌታም በእርሱ ላይ ያመፀውንና በኃጢያት የሞተውን አያድንም, ሞዛያ ፲፭፥፳፮. አምሊኪውያን በእግዚአብሔር ላይ አመጹ, አልማ ፫፥፲፰–፲፱. አመጸኞች በብዙ ሐዘን ይወጋሉ, ት. እና ቃ. ፩፥፫. የጌታ ቁጣ በአማጸኞቹ ላይ ነዷል, ት. እና ቃ. ፶፮፥፩ (ት. እና ቃ. ፷፫፥፩–፮). ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ ዐመፀ, ሙሴ ፬፥፫.