የጥናት እርዳታዎች
የነቢያት ትምህርት ቤት


የነቢያት ትምህርት ቤት

በከርትላንድ፣ ኦሀዮ (ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ) ውስጥ፣ በ፲፰፻፴፪–፻፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ክረምት፣ ስለ ወንጌል እና ስለእግዚአብሔር መንግስት በተመለከተ በሁሉንም ነገሮች ወንድሞችን ለማሰልጠን ጌታ ጆሴፍ ስሚዝን ትምህርት ቤት እንዲያደራጅ አዘዘው። ከዚህም ትምህርት ቤ ብዙዎቹ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች መጥተዋል። ሌላ የነቢያት ወይም የሽማግሌዎች ትምህርት ቤት በጃክሰን የግዛት ክፍል፣ ምዙሪ ውስጥ በፓርሊ ፒ ፕራት ተመራ (ት. እና ቃ. ፺፯፥፩–፮)። እንደዚህ አይነት ትምህርት ቤቶች ቅዱሳን ቀደ ምዕራብ ከተሰደዱ በኋላ ተጀምረው ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ ወዲያው እንዲቆሙ ተደረጉ። አሁን የወንጌል ትምህርት በቤት፣ በክህነት ስልታን ቡድኖች፣ እና በተለያዩ ደጋፊ ድርጅቶች፣ እንዲሁም በቤተክርስቲያኗ ትምህርት ቤቶች፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችና፣ በሀይማኖት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው የሚከናወኑት።