ካውደሪ፣ ኦልቨር ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ካህን እና ለመፅሐፈ ሞርሞን መለኮታዊ ስረ ነገርና እውነተኛነት ምስክር ከሆኑት ከሶስቱ አንዱ። ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ከወርቅ ሰሌዳዎች ሲተረጎም እንደ ጸሀፊ አገለገለ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፮–፷፰)። ስለመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም እውነትነት ምስክር ተቀበለ, ት. እና ቃ. ፮፥፲፯፣ ፳፪–፳፬. በመጥምቁ ዮሐንስ ተሾመ, ት. እና ቃ. ፲፫ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፰; ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፰–፸፫፣ የቁጥር ፸፩ ማስታወሻን ተመልከቱ). እውነትን ካገኘህ እና በአይኖችህ ካየሀቸው በኋላ፣ እንዳየሀቸው ትመሰክራለህ, ት. እና ቃ. ፲፯፥፫፣ ፭. በመንፈሴ የጻፍካቸው እውነት እንደሆኑ ለአንተ ገልጬልሀለሁ, ት. እና ቃ. ፲፰፥፪. በራዕያት ላይ ከመጋቢዎቹ አንዱ እንዲሆን ተመድቧልም ተሾሟልም, ት. እና ቃ. ፸፥፫. ከጆሴፍ ስሚዝ ጋር የክህነት ቁልፎችን ተቀብሏል, ት. እና ቃ. ፻፲.