መፅሐፈ ምሳሌ
አጭር የምግባረጥሩ አባባል ወይም ምክር።
መፅሐፈ ምሳሌ
አንዳንዶቹ በሰለሞን የተጻፉ ብዙ ምሳሌዎች፣ አባባሎች፣ እና ግጥሞች የያዘ የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ። መፅሐፈ ምሳሌ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በብዙ ጊዜ ተጠቅሷል።
ምዕራፍ ፩–፱ የእውነተኛ ጥበብ መግለጫን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፲–፳፬ ስለትክክለኛ ወይም ትክክል ስላልሆነ የመኖር መንገድ አባባል ጥርቅምን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፳፭–፳፱ የይሁዳ ንጉስ ሕዝቅያስ ሰዎች የመዘገቡትን የሰለሞን ምሳሌዎችን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፴–፴፩ የምግባረ ጥሩ ሴት መግለጫ ያለበት ነው።